ሐሙስ 2 ኖቬምበር 2023

Philippians 3፥20


“For our conversation is in heaven; from whence also we look for the Saviour, the Lord Jesus Christ:”  Philippians 3፥20 (KJV( ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕ 3:20 እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን ርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤

እኛ ክርስቲያኖች አገራችን በሰማይ የሆነ ለዚህችም ምድር
እንግዶች እና መፅአተኞች የሆንን ህዝቦች ነን
እኛ እንደ መስቀሉ ጠላቶች ትኩረታችን ምድራዊ ነገር ላይ
አይደለም የምንኖረውም ከምድር ጋር ተጣብቀን አይደለም
እኛ ልክ ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ እና ሙሽራዋም መጥቶ
እንዲወስዳት እንደምትናፍቅ ሴት
እኛም የክርስቶስን መምጣት የምንጠባበቅ በሰማይ
የተዘጋጀ ስፍራ ያለን ህዝቦች ነን

John 1፥14

And the Word was made flesh, and dwelt among us, (and we beheld his glory, the glory as of the only begotten of the Father,) full of grace and truth.”
  — John 1፥14 (KJV

መዳን በሌላ በማንም የለም

 


ህይወትህን መቀየር ከፈለክ






  If you want to change your life .....get into the Word.... there is no Shortcut....


ህይወትህን መቀየር ከፈለክ .....ወደ ቃሉ ግባ....አቋራጭ መንገድ የለም....

ወንጌል ምንድነው?




ወንጌል የሚለው ቃል በግሪክ እቫንጄሊዮን በመባል የሚታወቅ ሲሆን ትርጉሙም መልካም ዜና : የምስራች ቃል ማለት ነው። 


ድልን የሚያውጅ : ለልብ ደስታን የሚሰጥ መልዕክት ማለት ነው።


ወንጌል የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውሰጥ ከ98 በላይ ተጽፎ ይገኛል።


ወንጌል => በኀጢአት ምክንያት ከ እግዚአብሔር ተለይቶ የነበረው ሰው እግዚአብሔር የራሱ መፍትሔ መንገድ አዘጋጅቶ ወደ እራሱ ህብረት ለመመለስ ለ አዳምና ለሔዋን : ከዚያም ለአብርሃም : እንዲሁም ለእስራኤላውያን የገባውን ቃል ኪዳን በመሲሁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ በመፈጸም የዘላለም ሕይወት መንገድ ለሰዎች ሁሉ የከፈተበት የምስራች የሚያበስር ነው።


ወንጌል በአዲስ ኪዳን ብቻ የተገለጠ መልዕክት ሳይሆን የብሉ ኪዳን ቁልፍ መልዕክት ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ማንነት ተጠራጥሮ መልዕክተኞች ወደ ኢየሱስ በላከበት ጊዜ ኢየሱስ ስለራሱና ስለ መልዕክቱ የገለጠው ይህን እውነት ነበር።


ይህም መልዕክት የብሉ ኪዳን መካከለኛ መልዕክት ወንጌል እንደነበር (ማቲ 11:2-5) የሚገልጽ ነው። ነቢዩ ኢሳያስም በትንቢቱ የተናገረው ስለዚህ ወንጌል እንደነበር ኢየሱስ ራሱ በምድር ላይ አገልግሎት በጀመረበት ጊዜ ሲናገር እንዲህ አለ:-


"የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል " 

(ሉቃ 4: 17-19)