መንፈሱና ሙሽራይቱም ና ይላሉ። የሚሰማም ና ይበል።የተጠማም ይምጣ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” ራእይ 22፥17“And the Spirit and the bride say, Come. And let him that heareth say, Come. And let him that is athirst come. And whosoever will, let him take the water of life freely.”
ሐሙስ 2 ኖቬምበር 2023
Philippians 3፥20
“For our conversation is in heaven; from whence also we look for the Saviour, the Lord Jesus Christ:” Philippians 3፥20 (KJV( ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕ 3:20 እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን ርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤
ህይወትህን መቀየር ከፈለክ
If you want to change your life .....get into the Word.... there is no Shortcut....
ህይወትህን መቀየር ከፈለክ .....ወደ ቃሉ ግባ....አቋራጭ መንገድ የለም....
ወንጌል ምንድነው?
ወንጌል የሚለው ቃል በግሪክ እቫንጄሊዮን በመባል የሚታወቅ ሲሆን ትርጉሙም መልካም ዜና : የምስራች ቃል ማለት ነው።
ድልን የሚያውጅ : ለልብ ደስታን የሚሰጥ መልዕክት ማለት ነው።
ወንጌል የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውሰጥ ከ98 በላይ ተጽፎ ይገኛል።
ወንጌል => በኀጢአት ምክንያት ከ እግዚአብሔር ተለይቶ የነበረው ሰው እግዚአብሔር የራሱ መፍትሔ መንገድ አዘጋጅቶ ወደ እራሱ ህብረት ለመመለስ ለ አዳምና ለሔዋን : ከዚያም ለአብርሃም : እንዲሁም ለእስራኤላውያን የገባውን ቃል ኪዳን በመሲሁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ በመፈጸም የዘላለም ሕይወት መንገድ ለሰዎች ሁሉ የከፈተበት የምስራች የሚያበስር ነው።
ወንጌል በአዲስ ኪዳን ብቻ የተገለጠ መልዕክት ሳይሆን የብሉ ኪዳን ቁልፍ መልዕክት ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ማንነት ተጠራጥሮ መልዕክተኞች ወደ ኢየሱስ በላከበት ጊዜ ኢየሱስ ስለራሱና ስለ መልዕክቱ የገለጠው ይህን እውነት ነበር።
ይህም መልዕክት የብሉ ኪዳን መካከለኛ መልዕክት ወንጌል እንደነበር (ማቲ 11:2-5) የሚገልጽ ነው። ነቢዩ ኢሳያስም በትንቢቱ የተናገረው ስለዚህ ወንጌል እንደነበር ኢየሱስ ራሱ በምድር ላይ አገልግሎት በጀመረበት ጊዜ ሲናገር እንዲህ አለ:-
"የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል "
(ሉቃ 4: 17-19)
